በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞሮኮ ድጋሚ መንቀጥቀጥ ዛሬ ተከሰተ


ፎቶ ሮይተርስ (መስከረም 10፣ 2023)
ፎቶ ሮይተርስ (መስከረም 10፣ 2023)

በመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ፣ ሬክተር ስኬል፣ 6.8 የሚገመት የመሬት መንቀጥቀጥ ባለፈው ዓርብ ሞሮኮን ንጦ 2ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸውን ካጡ በኋላ፣ ዋናውን መንቀጥቀጥ ተከትሎ የሚመጣው መንቀጥቀጥ ዛሬ እሁድ ተከስቷል። በሬክተር ስኬል 3.9 እንደሚገመት ታውቋል።

የዛሬው መንቀጥቀጥ የተከሰተው የአደጋ ግዜ ሠራተኞች ከዓርቡ አደጋ የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ ባሉበት ወቅት ነው።

በሀገሪቱ በመቶ ዓመት ውስጥ የታየ ከባድ መንቀጥቀጥ ነው በተባለው አደጋ 300 ሺሕ ሰዎች ችግር ውስጥ ወድቀዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይገልጻል።

መንግስት በቂ የአደጋ ግዜ ሠራተኞችን ወደ አደጋው ሥፍራ አልላከም ሲሉ ሞሮኳውያን በማኅበራዊ ሚዲያ ቅሬታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።

“በፍርስራሹ ውስጥ ከነ ሕይወታቸው ያሉ ሰዎች አሉ። እነርሱን ለማዳን ምንም እያደረግን አይደለም” ሲሉ የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የአደጋ ሠራተኞች ቡድን መሥራች አርናኡድ ፍሬይስ ተናግረዋል። የቡድኑ ዓባላት ወደ ሞሮኮ ገብተው የነፍስ አድን ሥራ ለመሥራት ፓሪስ ላይ ሆነው ፈቃድ እየተጠባበቁ መሆኑም ታውቋል።

በአትላስ ተራራ ቁልቁለት ላይ ፍርስራሹ ውስጥ የተቀበሩ ቤተሰቦችን ጎረቤቶቻቸው ለማውጣት ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆኑ፣ የማራካሽ ከተማ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG