“ምርኩዝ”፥ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ ትምህርታቸውን በሚከታተሉ 18 ወጣቶች ከአንድ ዓመት በፊት የተቋቋመ የሕክምና ተማሪዎች ተነሣሽነት ነው፡፡
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች የኾኑት የምርኩዝ መሥራቾች፣ የሕሙማኑንና የአስታማሚዎቻቸውን የስሜት ጫና ለማከም፣ ለሕሙማኑ የሚያስፈልጉ እንደ ዳይፐር፣ ፍራፍሬ፣ የሕፃናት መጫወቻዎች የመሳሰሉ ግብዓቶችን እንደ ቤተሰብ እያቀረቡ ይጠይቃሉ፡፡
የምርኩዝ ተነሣሽነት ሥራ አስኪያጅ እና የሕክምና ተማሪው አቤኔዘር አብዮት፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርጓል፡፡
መድረክ / ፎረም