በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመቐለ የጠሩት ሰልፍ በኀይል ተበተነ


ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመቐለ የጠሩት ሰልፍ በኀይል ተበተነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:31 0:00

ሦስት የትግራይ ክልላዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ “ኪዳን ለሥር ነቀል ለውጥ” በሚል መሪ ቃል፣ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በመቐለ ከተማ የጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የጸጥታ ኀይሎች ተበተነ፡፡

ሰልፉ በኀይል ርምጃ ሲበተን፣ በሰላማዊ ሰዎች እና በብዙኀን መገናኛ ዘጋቢዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ እና ማንገላታት እንደተፈጸመ፣ ከ150 በላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ አመራሮች እና የሰልፉ ተሳታፊዎች ደግሞ እንደታሰሩ፣ የውድብ ናፅነት ትግራይ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ዓለምሰገድ አረጋይ ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከመቐለ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት፣ በአካል ቀርበን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

ኾኖም፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት፣ ትላንት በሰጡት መግለጫ፣ ሰልፍ መውጣት ማሳወቅ እንጂ ማስፈቀድ የማያስፈልገው ሕገ መንግሥታዊ መብት ቢኾንም፣ በክልሉ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት በመኖሩ፣ ቦታው እና ጊዜው እንዲቀየር፣ ከፓርቲዎቹ አመራሮች ጋራ እየተነጋገሩ እንደኾኑ ገልጸው ነበር፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG