በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በቡድን 20 ጉባኤ ላይ እንዳልተጋበዘ ገለጸ


የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት፣ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት፣ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

አዲሱ የቡድን 20 የበለጸጉ ሀገራት ዓባል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ኅብረት፣ ቡድኑ በሳምንቱ መጨረሻ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ እንዳልተጋበዘ ገልጿል።

ነገ ዓርብ እና ቅዳሜ በኒው ደሊ የሚካሄደውን ጉባኤ ያዘጋጀችው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ አፍሪካዊው ድርጅት ቡድኑን እንዲቀላቀል ጥሪ አድርገው ነበር።

የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ቃል አቀባይ የሆኑት ኤባ ካሎንዶ፣ ኅብረቱ በጉባኤው ላይ እንዲገኝ ጥሪ እንዳልደረሰው ትናንት ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

19 ሀገራትን እና የአውሮፓ ኅብረትን በዓባልነት ያቀፈው ስብስብ፣ 85 በመቶ የዓለምን የሀገር ውስጥ ምርት እና ከዓለም ሕዝብ ሁለት ሶስተኛውን ይይዛል።

ደቡብ አፍሪካ ከአህጉሪቱ ብቸኛዋ የቡድኑ ዓባል ነች፡፡

“የአፍሪካ ኅብረትን የጋበዝነው ወደፊት ቋሚ ዓባል እንዲሆን ታሳቢ በማድረግ ነው” ሲሉ ሞዲ ከ 10 ቀናት በፊት ተናግረው ነበር።

“የአፍሪካ ኅብረትን በቋሚ ዓባልነት ሞቅ አድርገን ለመቀበል እንጠብቃለን” ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ባለፈው ታህሳስ ተናግረው ነበር፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG