ዘንድሮ የዓለም የሴቶች እግር ኳስ ጨዋታ አሸናፊ የሆነው የስፔይን ቡድን ተጫዋች ጄኒ ሄርሜሶ የአገሪቱን የእግር ኳስ የፌድሬሽን ፕሬዚዳንት በወሲብ ትንኮሳ እንደምትከሳቸው የስፔይን አቃቤ ህግ ዛሬ አስታወቀ፡፡
ሄርሜሶ ክሱን የመሠረተቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቤለስ በሴቶቹ የእግር ኳስ ዋንጫ ፍጻሜ ላይ ደስታቸውን ለመግለጽ ያለፈቃድዋ ከንፈሯ ላይ በመሳማቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
ባላፈው ነሀሴ ወር መገባደጃ ላይ፣ የአለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ፣ የፕሬዚዳንቱ "የዲሲፕሊን ጉዳይ እስኪታይ ድረስ" በሩቤለስ ላይ የ90 ቀናት እገዳ ጥሏል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቤለስ የተፈጠረው መሳሳም በፈቃደኝነት ላይ የተደረገ መሆኑን በመግለጽ ከሥልጣናቸው ለመነሳት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የስፔይን ፖለቲከኞች እና አንዳንዶቹ የአገሪቱ ዝነኛ የእግር ኳስ ክለቦች የፕሬዚዳንቱን ድርጊት አውግዘዋል፡፤
የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ሁለት ኃላፊዎች ድርጊቱን በመቃወም በገዛ ፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸው ተገልጿል፡፡
መድረክ / ፎረም