በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳዬል ለሙከራ ተኮሰች


ፋይል - በታይዋን፣ ፒንግተንግ ከተማ በተካሄደ ልምምድ፣ አንድ የታይዋን ወታደር አሜሪካ ሰር የሆነ ሚሳዬል ሲያስወነጭፍ - ሐምሌ 4፣ 2023
ፋይል - በታይዋን፣ ፒንግተንግ ከተማ በተካሄደ ልምምድ፣ አንድ የታይዋን ወታደር አሜሪካ ሰር የሆነ ሚሳዬል ሲያስወነጭፍ - ሐምሌ 4፣ 2023

ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ ረቡዕ ሚኒትማን ሶስተኛ የተሰኘውን አህጉር አቋራጭ ተወንጫፊ የባለስቲክ ሚሳዬል ለሙከራ መተኮሷን የአገሪቱ ጦር አስታወቀ፡፡

ይህ ሙከራ የዩናይትድ ስቴትስ የኒውክሌር መከላከያ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ እና ውጤታማ መሆኑን ለማሳየት የታቀዱ የዕለት ተዕለት እና ወቅታዊ ተግባራት አካል ነው" ሲል የአሜሪካ አየር ኃይል ዓለም አቀፍ እዝ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

እንዲህ አይነት ሙከራዎች ከዚህ በፊት ከ300 ጊዜ በላይ ተካሂደዋል፤ ይህ ፍተሻ ለአሁን ዓለም አቀፍ ወቅታዊ ክስተቶች ምላሽ አይደለም" ሲልም መግለጫው አክሏል።

ፔንታገን ዛሬ ጧት በካሊፎርኒያ በሚገኘው የቫንደንበርግ የጠፈር ኃይል ጣቢያ የተደረገው ሙከራ ለዓመታት መታቀዱን ገልጾ የሩሲያ መንግሥትም ስለ እቅዶቹ የተነገረው መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡

ዘሚኒማን ሶስተኛ ለ50 ዓመታት ያገለገለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከዩናይትድ ስቴትስ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎች ውስጥ፣ መሠረቱን መሬት ላይ ያደረገ ብቸኛው አህጉር አቋራጭ ተወንጫፊ የባለስቲክ ሚሳዬል መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ይህም ከትሪደንት ባህር ሰርጓጅ የጦር መከርብ ላይ የሚወነጨፉ እና በስትራቴጂክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የሚጫኑ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን የሚያካትት መሆኑ ተነግሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG