ከፍተኛ ወጭ አውጥተው እንደተማሩ የሚናገሩ አስተያየት ሰጭ “ዘንድሮ ተመርቄ በምሰራበት ተቋም የደረጃ እድገት የማገኝበት፣ ለመጭው ዓመት ደግሞ ለሌላ የትምህርት ደረጃ የምዘጋጅበት ዕድል አልፎኛል” ብለዋል፡፡
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በጦርነቱና በሌሎች ችግሮች ሳቢያ መመረቅ የሚገባቸው ብቻ ሳይሆኑ በትምህርት ላይ ያሉትም ለተጨማሪ ዓመት ትምህርታቸው መራዘሙን ጠቅሷል፡፡
በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምጽ ምላሽ የሰጡት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት የመምህራንና ተማሪዎች ልማት ክፍል ኃላፊ የትምህርት ጥራትን ዕውን ለመድረግ ሲባል ውሳኔው መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡
የአማራ ክልል መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማኅበር ግን “ውሳኔውን ድንገት ከማውረድ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ሊደረግበት ይገባ ነበር” ሲል ቅሬታውን አሰምቷል፡፡
(ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ)