በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጭ ማኅቀፎች ግብዓት ማሰባሰቡ እንደተጠናቀቀ ተገለጸ


ለሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጭ ማኅቀፎች ግብዓት ማሰባሰቡ እንደተጠናቀቀ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:33 0:00

በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አማራጭ ማኅቀፎች ላይ፣ ከዐዲስ አበባ ከተማ በቀር ከኹሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሕዝብ ግብዓት የማሰባሰብ ሥራው እንደተጠናቀቀ፣ ቡድኑ አስታወቀ፡፡ ከ12 ክልሎች እና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከማኅበረሰቡ በርካታ ግብዓት እንደተገኘ የገለጹት የብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ የባለሞያዎች ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ታደሰ ካሳ፣ ፖሊሲው በሳምንታት ውስጥ እንደሚዘጋጅ አመልክተዋል፡፡

በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያለው የትጥቅ ግጭት፣ የፖሊሲ ግብዓቱን በማሰባሰብ ሒደት ላይ ጫና እንደፈጠረ የገለጹት የቡድኑ አባል ዶክተር ማርሸት ታደሰ፣ በዚኽም ምክንያት ያልተሸፈኑ ሥፍራዎች መኖራቸውን አልሸሸጉም፡፡

የሽግግር ፍትሕ ሒደቱ፣ ከኹሉን አቀፍ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ጋራ ስላለው ልዩነት እና አንድነትም፣ ባለሞያዎቹ አብራርተዋል፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)

XS
SM
MD
LG