በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዋሽ አርባ እስረኞችን ማግኘት ያልቻሉ ቤተሰቦቻቸው ደኅንነታቸው እንደሚያሳስባቸው ገለጹ


የአዋሽ አርባ እስረኞችን ማግኘት ያልቻሉ ቤተሰቦቻቸው ደኅንነታቸው እንደሚያሳስባቸው ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00

በአማራ ክልል ላይ ከተላለፈውና እንዳስፈላጊነቱ በሌሎችም አካባቢዎች እንደሚፈጸም ከተገለጸው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጋራ በተያያዘ፣ ወደ አዋሽ አርባ ተወስደው የታሰሩ ቤተሰቦቻቸው ደኅንነት እንደሚያሳስባቸው፣ የእስረኞቹ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

እስረኞቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ መገናኘት እንዲችሉ ከፖሊስ ጋራ መግባባት ላይ እንደተደረሰ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ቢያስታውቅም፣ እስከ አኹን እንዳላገኟቸው አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሥራ ክፍል ከፍተኛ ዲሬክተር ዶር. ሚዛኔ አባተ፣ ከፖሊስ ጋራ ተደርሶበታል የተባለውን መግባባት አፈጻጸም ኮሚሽኑ እንደሚከታተል አስታውቀዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያይዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG