በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘ሀገራቹ ትደግፋችኋለች’ ሲሉ ባይደን በማዕበል ለተጎዱ የፍሎሪዳ ነዋሪዎች ቃል ገቡ


ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በፍሎሪዳ ጉብኝት ላይ ነኅሴ 2015
ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በፍሎሪዳ ጉብኝት ላይ ነኅሴ 2015

ትላንት ቅዳሜ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በአውሎ ነፋስ ኢዳሊያ ጉዳት የደረሰባቸውን የፍሎሪዳ ከተሞች ጎበኙ። ፕሬዘዳንቱ ከአውሮፕላናቸው ሳይወርዱ ጉዳት የደረሰባቸውን ስፍራዎች እንዲቃኙ የተደረገ ሲሆን በኋላም ወርደው ጎብኝተዋል። ይሁን እንጂ የፍሎሪዳ አገረገዥ የሆኑት ሪፐብሊካኑ ደሳንቲስ በአካባቢው የዴሞክራቶች መገኘት የአደጋ ጊዜ ምላሽ ላይ ችግር ይጋርጣል በማለት በስፍራው ሳይገኙ ቀርተዋል።

ባይደን የተቀናቃናቸውን ምላሽ በተመለክተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሁኔታው እንዳልተበሳጩ ገልጸው በግዛቱ ከሚገኙ ከሁለቱ የሪፐብሊካን ሴኔተሮች አንዱ በሆኑት ሪክ ስኮት አቀባበል ቤተኝነት እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

ፕሬዘዳንቱ አያይዘውም ፌድራል መንግስት ሙሉ ለሙሉ ለፍሎሪዳ ነዋሪዎች ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG