በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ተ.መ.ድ በ21ኛው ክፍለዘመን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች እንዲያሻሽል ጥሪ አደረጉ


የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንዲራ ሞዲ
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንዲራ ሞዲ

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ዛሬ እሁድ ህትመት ላይ በዋለ ቃለ መጠይቃቸው የተባበሩት መንግስታት ውክልና ሊገባቸው የሚገባቸው ድምጾች ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግ ጥሪ አድርገዋል።

የቡድን 20 ባለጸጋ ሀገራትን በቀጣዩ ሳምንት የሚቀበሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ “የ20ኛው ክፍለ ዘመን አካሄድ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን አያገለግልም” ሲሉ ተናግረዋል።

እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላትን ሀገር እየመሩ ያሉት ሞዲ ሀገራቸው ህንድ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክርቤት አባል እንደትሆን ሀሳብ አላቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንኑ ዕቅዳቸውን በመጭው የቡድን 20 ሀገራት የመሪዎችን ስብሰባ ላይ እንደሚገቡበት ይጠበቃል።

ሞዲ አፍሪካ ህብረት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክርቤት የሙሉ ጊዜ አባል እንዲሆን መጠየቃቸውንም እንደሚገፉበት ይጠበቃል።

"አለምአቀፍ ተቋማት ተለዋዋጭ እውነታዎችን መገንዘብ አለባቸው:: ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች እንደገና ማጤን አለባቸው" ያሉ ሲሆን አክለውም "ህንድ የቡድን 20 ሀገራት ፕሬዘደንት መሆኗ ሥስተኛው አለም እየተባሉ በሚጠሩ ሀገራትም ዘንድ የመተማመንን ዘር ዘርቷል።" ሲሉ ውክልና መኖሩ ያለውን ጠቀሜታ አስረድተዋል።

በተጨማሪም ሞዲ የሳይበር ደህንንነት ወንጀልን ለመከላከል አለም አቀፍ ጥረት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG