በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያው የኑሮ ውድነቱን እንዳያባብሰው አስግቷል


የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያው የኑሮ ውድነቱን እንዳያባብሰው አስግቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:39 0:00

የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያው የኑሮ ውድነቱን እንዳያባብሰው አስግቷል

መንግሥት፣ በያዝነው ሳምንት ከነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማሻሻያ፣ የኑሮ ውድነቱን እንደሚያባብሰው፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የዐዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በነዳጅ ላይ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ፣ በሌሎችም ሸቀጦች ላይ ቀጥተኛ ጫና እንደሚሳድር፣ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

የኢኮኖሚ ባለሞያው ዶር. አደም ፈቶ በበኩላቸው፣ መንግሥት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንዲያደርግ የሚያስገድዱ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ምክንያቶች እንዳሉ ጠቅሰው፣ የዋጋ ማሻሻያው፣ የሌሎች ሸቀጦችን ዋጋ የማናር ተጽእኖ ይኖረዋል፤ ብለዋል፡፡ ከነዳጅ ዋጋ መጨመር ጋራ ተያይዘው የሚመጡ ጫናዎችን ለመቀነስም፣ የአጭር እና የረዥም ጊዜ ርምጃዎችን መውሰድ እንደሚጠበቅበት አመልክተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG