በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታገደው የማኅበረ ረድኤት ትግራይ ቦርድ ተቋሙን የማስተዳደር ሥልጣኑን ተረከበ


የታገደው የማኅበረ ረድኤት ትግራይ ቦርድ ተቋሙን የማስተዳደር ሥልጣኑን ተረከበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:38 0:00

የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ፣ ከህወሓት ጋራ ግንኙነት አላቸው፤ በሚል እግድ ከተጣለባቸው ድርጅቶች አንዱ ማኅበረ ረድኤት ትግራይ/ማረት/፣ በባለአደራ ቦርድ ተይዞ የቆየውን ተቋሙን የማስተዳደር ሥልጣን መልሶ እንደተረከበ አስታወቀ፡፡ የማኅበረ ረድኤት ትግራይ ጊዜያዊ ዲሬክተር አቶ ጌታቸው ካልአዩ፣ የተቋሙ የቀድሞ ቦርድ፣ ወደ ሥራው ለመመለስ እየተዘጋጀ እንደኾነ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ማኅበረ ረድኤት ትግራይ እና የትግራይ ልማት ማኅበር የሚገኙባቸው ስድስት ድርጅቶች፣ የተጣለባቸው እግድ እንዲነሣ የወሰነው ባለፈው ወር ነበር፡፡

በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት፣ ከህወሓት ጋራ ግንኙነት አላቸው ተብለው በተጠረጠሩ ድርጅቶች ላይ በፍርድ ቤት ተጥሎ የነበረው እግድ በመነሳት ላይ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ታስረው የነበሩ የህወሓት አመራሮችም በዚኹ ስምምነት መሰረት ተፈተዋል፣ የተለያዩ ክሶችም ተቋርጠዋል፡፡ ሆኖም፣ በስምምነቱ መሰረት ያልተፈፀሙት ተግባራት ይበዛሉ ይላሉ፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲው የህግ መምህር አቶ መኮንን ፍሰሀ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ፣ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ከፌደራሉ መንግስት ጋራ እየተነጋገረ ስለመሆኑ ይገልፃል፡፡

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)

XS
SM
MD
LG