በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋቦን የኦማር ቦንጎ ታማኝ የነበሩት ጀኔራል መሪነቱን ተቆናጠዋል


የጋቦን አዲሱ መሪ፣ ጀኔራል ብሪስ ኦሊጉዊ ንግዌማ፣ ወታደሮች ተሸክመዋቸው በመዲናዋ ሊበርቪል ሲጨፍሩ ይታያል (ፎቶ AP ነሐሴ 30፣ 2023)
የጋቦን አዲሱ መሪ፣ ጀኔራል ብሪስ ኦሊጉዊ ንግዌማ፣ ወታደሮች ተሸክመዋቸው በመዲናዋ ሊበርቪል ሲጨፍሩ ይታያል (ፎቶ AP ነሐሴ 30፣ 2023)

በጋቦን በትናንትናው ዕለት በመፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱን መሪ አሊ ቦንጎ ከስልጣን ያሰውገዱት ጀኔራሎች፣ የአባታቸው ኦማር ቦንጎ ታማኝ የነበሩትን ጀኔራል አዲስ መሪ አድርገው መርጠዋል።

የቀድሞ የሪፐብሊካን ዘቡ የደህንነት አለቃ የነበሩትና፣ አሁን የሀገሪቱ መሪ ሆነው የተሾሙት፣ ጀኔራል ብሪስ ኦሊጉዊ ንግዌማ፣ ለረጅም ዘመን የሀገሪቱ መሪ የነበሩት ኦማር ቦንጎ የቅርብ ታማኝ አገልጋይ እንደነበሩ ተነግሯል።

ለ 42 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት ኦማር ቦንጎ፣ እ.አ.አ 2009 በሞት ተለይተው ስለጣኑን ልጃቸው አሊ ቦንጎ ሲረከቡ፣ ጀኔራል ብሪስ ኦሊጉዊ ንግዌማ ገለል ተደርገው፣ በሞሮኮ እና በሴኔጋል የኤምባሲ አታሼ በመሆን ሲሠሩ ቆይተዋል። ከእ.አ.አ 2018 ጀምሮ ደግሞ የሪፐብሊካን ዘቡ የደህንነት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

ባለፈው ቅዳሜ በተደረገ አጨቃጫቂ ምርጫ 64.27 ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል የተባሉትን አሊ ቦንጎ ከስልጣን ያስወገዱት የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ጀኔራሎች፣ ትናንት በቴሌቭዥን ቀርበው ዜናውን ሲያበስሩ፣ ጀኔራል ብሪስ ኦሊጉዊ ንግዌማ አልተገኙም ነበር።

ብዙም የማያወሩና እና ሚስጥራዊ ናቸው የተባሉትን አዲሱ መሪ፣ ትናንት ወታደሮች ተሸክመዋቸው ሲጨፍሩ ተስተውሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG