በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጆሃንስበርግ በሕንጻ ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ ከ 70 በላይ ሠዎች ሞቱ


ፎቶ ሮይተርስ (ነሐሴ 31፣ 2023)
ፎቶ ሮይተርስ (ነሐሴ 31፣ 2023)

በጆሃንስበርግ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ በአንድ ሕገ ወጥ መኖሪያ ነው በተባለ ባለ 5 ፎቅ ሕንጻ በተከሰተ የእሳት አደጋ፣ ሕጻናትን ጨምሮ ከ 70 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የከተማው የአደጋ አገልግሎት አስታውቋል።

በሌሊት ከተነሳው እሳት ለማምለጥ በአደጋ ግዜ መውጪያው በኩል ለመውጣት የሞከሩት ነዋሪዎች በሩ ባለመከፈቱ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአደጋ ግዜ ሠራተኞች በሩን በከፈቱበት ወቅት በርካታ አስከሬኖች በበሩ አቅራቢያ ተከማችቶ ማግኘታቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በአደጋው ከ 50 በላይ ሠዎች መጎዳታቸውም ታውቋል።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎች በብዛት በሚኖሩበት እና በርካታ ወንጀልም ይፈጸምበታል በተባለ የከተማዋ ክፍል የሚገኘው ሕንጻ፣ የተተወ እና በሕገ ወጥ መኖሪያነት ሲያገለግል ነበር ተብሏል።

ከሕንጻው ነዋሪዎች አብዛኞቹ የውጪ ሀገር ዜጎች ነበሩ ሲሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል። ከሟቾቹ ቢያንስ ሰባቱ ሕጻናት መሆናቸውን እና አንድ የሁለት ዓመት ሕጻንም እንዳሚገኝበት ነዋሪው ጨምረው ገልጸዋል። አንዳንዶቹ መለየተ በማይችሉበት ደረጃ ተቃጥለዋል ሲሉ አክለዋል።

የአሳቱ መንስሄ ለግዜው አልታወቀም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG