የአል-ቡርሃን የግብጽ ጉብኝት፣ ጦርነቱ በሱዳን ከተጀመረበት ካለፈው ሚያዝያ ወር ወዲህ፣ የመጀመሪያው የውጪ ሀገር ጉብኝት ነው፤ ተብሏል። ጀነራሉ፣ በግብጹ አል-ሲሲ፣ ለአንድ ሀገር መሪ የሚደረግ የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ ሠራዊታቸው፣ ለብቻው ሥልጣንን የመቆጣጣር ፍላጎት እንደሌለው የገለጹት አል ቡርሃን ተናግረዋል። ዋናው ግባቸውም፣ ለአራት ወራት የቆየውን ጦርነት በአስቸኳይ ማቆም እንደኾነ አክለዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ)