በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ድሮኖች ወደ ሩሲያ ግዛት ጠልቀው ጥቃት እያደረሱ ነው


አንድ የዩክሬን ወታደር፣ በዶኔትስክ አቅራቢያ ባለው መስመር በሩሲያ በተያዙ ቦታዎች ላይ ያነጣጠረ ፀረ-ታንክ ሮኬት ማስወንጨፊያ ያዘጋጃል - ነሐሴ 19፣ 2023
አንድ የዩክሬን ወታደር፣ በዶኔትስክ አቅራቢያ ባለው መስመር በሩሲያ በተያዙ ቦታዎች ላይ ያነጣጠረ ፀረ-ታንክ ሮኬት ማስወንጨፊያ ያዘጋጃል - ነሐሴ 19፣ 2023

ዩክሬን በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) በምሽት አሰማርታ ምዕራብ ሩሲያ የሚገኙ ወታደራዊ ይዞታዎችን ማጥቃቷን የሩሲያ ባለሥልጣናት እና የዜና አውታር ዘገባዎች አመለከቱ።

የሩሲያ የዜና አገልግሎት የሆነው ታስ እንደዘገበው፣ ድሮኖቹ ሩሲያን ከኢስቶኒያና ላቲቪያ ከሚያዋስናት ድንበር አቅራቢያ ያለውን አውሮፕላን ማረፊያ አጥቅተዋል። በጥቃቱም ከፍተኛ ቃጠሎ የተነሳ ሲሆን አራት የጦር ሟጓጓዣ አውሮፕላኖች መጎዳታቸውን ዘግበዋል።

ዛሬ ረቡዕ ጧት በተካሄደው ድብደባ ምንም እንኳ በሰው ላይ ያደረሰው ጉዳት መኖሩ ባይገለጽም፣ ከ18 ወራት በፊት ከተጀመረው የዩክሬን ጦርነት ወዲህ፣ በሩሲያ ምድር የተፈጸመ ትልቁ የድሮን ጥቃት መሆኑን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የዩክሬን ባለሥልጣናት ሩሲያ ምሽቱን ባካሄደችው ከባድ እና የተቀናጀ ጥቃት ኪቭን በድሮኖችና ሚሳዬሎች በመደብደብ ሁለት ሰዎች መግደሏን አስታውቀዋል።

ዩክሬን የሞስኮን ኃይል ለማስወጣት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በመጀመሯ ሩሲያ ላይ የሚደርሰው የአየር ላይ ጥቃት መባባሱ ተዘግቧል።

ኪየቭ በምስራቅ እና በደቡባዊ ዩክሬን የግንባር መስመሮች በስተጀርባ ባሉት የሩሲያ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እያካሄደች መሆኑም በአሶሴይትድ ፕሬስ ተመልክቷል።

በጥቁር ባህር ላይ የሚገኙ የሩስያ መርከቦችንም ለማጥቃት የባህር ኃይል ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) መጠቀሟን ዩክሬን አስታውቃለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG