በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ በሻራ ቀበሌ ከተፈጠረው ግጭት እና ግድያ ጋራ በተያያዘ፣ ሰዎች እንደታሰሩ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ቤተሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
የሻራ ቀበሌን እንዲያስተዳድሩ የተሾሙ ግለሰቦች፣ ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ በተቃወሙ ነዋሪዎች እና በመንግሥት የጸጥታኀይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት፣ ሰዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ፣ ከትላንት በስቲያ መዘገባችን ይታወሳል።
በሌላ በኩል፣ የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)፣ “መንግሥት ተመጣጣኝ ያልኾነ የኀይል ርምጃ ወስዷል፤” ሲልክሥ አሰምቷል።
የጋሞ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽንስ መምሪያ ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ሙከራ፣ ለጊዜው አልተሳካም።
ኖም መምሪያው፣ የዞኑን የጸጥታ ግብረ ኀይል ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ፣ የታጠቀን ኀይል በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሲባል በተወሰደ ርምጃ፣ የሰው ሕይወት እንዳለፈና ንብረትም እንደወደመ ማስታውቁ ይታወሳል። ዝርዝር ዘገባውንከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም