በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ወደ ኬንያና ኢትዮጵያ ይጓዛሉ


የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር
የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 8/2015 ወደ ናይሮቢ እና አዲስ አበባ እንደሚጓዙ ተገለጸ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ፣ ሐመር ከኬንያ እና ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት፣ ከአፍሪካ ኅብረት፣ ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋራ ይገናኛሉ ብሏል።

ሐመር በቆይታቸው ሱዳን ስላለው ቀውስ እና ሁከቱን ለማስቆም፣ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማስፈን፣ ፍትህ እና ተጠያቂነትን ለመደገፍ በሚደረገው አህጉራዊ እና አለም አቀፍ ጥረቶች ዙሪያም እንደሚወያዩ መግለጫው አመልክቷል።

በኢትዮጵያ ግጭትን ማስቆም፣ ስምምነትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ፣ የዜጎችን ደህንነት ስለመጠበቅ አሳሳቢነት ፣እንዲሁም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በድርድር ለመፍታት በሚቻልባቸው መንገድ ይወያያሉ ሲልም የሚኒስቴሩ መግለጫ አስታውቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG