በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህንድ ጠ/ሚኒስትር የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 ሀገራትን እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረቡ

"ቋሚ አባልነት በመስጠት ራዕይ ውስጥ ለአፍሪካ ህብረት ግብዣ አቅርበናል " ሲሉ ሞዲ ቢ20 የተሰኘው በቢዝነስ ፎረም እና የመስከረም ወሩ ጉባዔ መዳረሻ መድረክ ላይ ተናግረዋል ።
"ቋሚ አባልነት በመስጠት ራዕይ ውስጥ ለአፍሪካ ህብረት ግብዣ አቅርበናል " ሲሉ ሞዲ ቢ20 የተሰኘው በቢዝነስ ፎረም እና የመስከረም ወሩ ጉባዔ መዳረሻ መድረክ ላይ ተናግረዋል ።

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 አባል እንዲሆን በዛሬው ዕለት ጥሪ አቅርበዋል ። በሚቀጥለው ወር በኒው ዴሊ ከሚካሄደው የቡድኑ መሪዎች ጉባኤ መዳረሻ በተሰማው ንግግራቸው የዓለም አቀፉ የአቅርቦት ሰንሰለት ችግሮችን ለመቅረፍ ሀገራቸውን እንደመፍትሔ አቅርበዋል ።

የ20 ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ስሪት የሆነው ቡድን 19 አገሮችን እና የአውሮፓ ህብረትን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን ፣ 85 በመቶውን ዓለም አቀፉ ጥቅል የሀገራት ምርት መጠን እና ከዓለም ህዝብ መካከል ደግሞ ሁለት ሶስተኛውን ይሸፍናል ።ይሁንና ከአህጉረ አፍሪካ የህብረቱ ብቸኛ አባል ደቡብ አፍሪካ ናት።

በታህሳስ ወር የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 ሀገራት G20 ቡድንን በቋሚ አባልነት እንዲቀላቀል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት የወቅቱ የቡድኑ ጉባዔ አስተናጋጅ ሀገር ህንድ መሪ ሞዲ ባለፈው አመት በአጠቃላይ 3 ትሪሊዮን ዶላር አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ያስመዘገበው ፓን- አፍሪካዊ ህብረት በቡድኑ አባልነት እንዲካተት ጥሪ አቅርበዋል።

"ቋሚ አባልነት በመስጠት ራዕይ ውስጥ ለአፍሪካ ህብረት ግብዣ አቅርበናል " ሲሉ ሞዲ ቢ20 የተሰኘው በቢዝነስ ፎረም እና የመስከረም ወሩ ጉባዔ መዳረሻ መድረክ ላይ ተናግረዋል ።

መቀመጫውን በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት 55 አባላት ያሉት ሲሆን በወታደራዊ አስተዳደር ስር የሚገኙ አምስት ሀገራት ግን በአሁኑ ጊዜ ከአባልነት ታግደዋል።

ሞዲ በተጨማሪም ህንድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የተስተጓጎለውን ውጤታማ እና አስተማማኝ ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ለመፍጠር ሀገራቸው “መፍትሔ” እንደሆነች ገልፀዋል ። ኒው ዴሊ ከቻይና ጋር ለመወዳደር አምራችነቷን ለማጠናከር እየሰራች እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG