በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋሞ ዞን በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት ጠፋ


በጋሞ ዞን በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት ጠፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:00 0:00

በጋሞ ዞን አርባምጭ ዙርያ ወረዳ፣ ሻራ ቀበሌ በተፈጠረ ግጭት ከትናንት ጀምሮ 18 ሰዎች መገደላቸውን እና 20 ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። አንድ የአርባምንጭ ሐኪም በበኩላቸው 12 ሰዎች መሞታቸውን እና 15 መቁሰላቸውን ለአሜሪካ ድምጽ አረጋግጠዋል። የዞኑ ኮሙኒኬሽንስ ጉዳዮች መምሪያ ባወጣው መግለጫ ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ለማፍረስ የሞከረውን ታጣቂ ኃይል በቁጥጥር ስር ለማዋል በተወሰደ እርምጃ የሰው ህይወት ማለፉን አስታውቋል።


በጋሞ ዞን አርባምጭ ዙርያ ወረዳ፣ ሻራ ቀበሌ በተፈጠረ ግጭት ከትናንት ጀምሮ 18 ሰዎች መገደላቸውን እና 20 ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

አንድ የአርባምንጭ ሐኪም በበኩላቸው 12 ሰዎች መሞታቸውን እና 15 መቁሰላቸውን ለአሜሪካ ድምጽ አረጋግጠዋል።

የዞኑ አስተዳደር መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የዞኑን የፀጥታ ግብረ ኃይል ጠቅሶ ባወጣው መግለጫም፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ለማፍረስና የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ለማደፍረስ የታጠቀውን ኃይል በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲባል በተወሰደው እርምጃ "መጠነኛ" ያለው የሰው ህይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን አስታውቋል።

የአከባባው ነዋሪዎች ግን መንግሥት ራሱ አሰልጥኖ መሳሪያ የሰጣቸው የቀበሌ ታጣቂዎች እንጂ የታጠቀ ቡድን የለም ሲሉ አስተባብለዋል።

የግጭቱ መንስኤ የሻራ ቀበሌን ከአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ተነጥሎ ወደ አርባምንጭ ከተማ እንዲካለል በመወሰኑ ነው ሲሉ አንድ የዓይን እማኝ እና የቀበሌው ነዋሪ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

እኚኹ አስተያየት ሰጪ ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ በተፈጠረው አለመግባባት ቀበሌው ለወራት ከመንግሥታዊ አገልግሎት ውጭ ኾኖ መቆየቱንም ገልፀዋል።

የሰው ህይወት ወደጠፋበት ግጭት ያመራው ግን ቀበሌውን ወደ ስራ ለማስገባት የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር እና የአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ የፀጥታ ሃይሎች ወደ ቀበሌው በመግባታቸው እና የሻራ ቀበሌ ሚሊሻዎች፣ ወጣቶች እና የቀበሌው ነዋሪዎች ጋር ምክክር አድርገው በመተማመን ላይ ሳይደረስ በመቅረቱ ነው ብለዋል። ነዋሪው "የኛ ቀበሌ ወደ አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር አይካለልም" ማለቱንም አመልክተዋል።

ሌላ ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሆስፒታል ሐኪም፣ 12 ሰዎች በጦር መሳሪያ መገደላቸውን እና፣ በልዩ ልዩ አካላቸው ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው የመጡ 15 ቁስለኞች እየታከሙ መኾናቸውን ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG