በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመቐለ በመዝናኛ ስፍራ ላይ የተወረወረ ቦምብ የሕይወት እና የአካል ጉዳት አደረሰ


በመቐለ በመዝናኛ ስፍራ ላይ የተወረወረ ቦምብ የሕይወት እና የአካል ጉዳት አደረሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:47 0:00

በመቐለ በመዝናኛ ስፍራ ላይ የተወረወረ ቦምብ የሕይወት እና የአካል ጉዳት አደረሰ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ፣ ቐዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ፣ “ዳዕሮ” በተባለ የምሽት መዝናኛ ቦታ፣ ትላንት በተወረወረ የእጅ ቦምብ፣ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

የተጣላትን ፍቅረኛውን በምሽት መዝናኛው ከሌላ ሰው ጋራ ኾና የተመለከተው የተሰናበተ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊ ተጠርጣሪ በቅናት ተነሣስቶ ድርጊቱን መፈፀሙን ፖሊስ አስረድቷል።

የአሸንዳ በዓል የመጨረሻው ቀን በሚከበረበት፣ ትላንት፣ ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ሌሊት 8 ሰዓት ገደማ፣ የተወረወረው የእጅ ቦምብ በ20 ሰዎችም ላይ የአካል ጉዳት ማድረሱን የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ወልዳይ ማውጫ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

የጥቃት አድራሹ ተጠርጣሪ ማንነት እንደታወቀ የፖሊስ አዛዡ ቢያስታውቁም፣ ገና በቁጥጥር ሥር እንዳልዋለ ገልጸዋል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG