በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዚምባብዌ ምርጫ በአንዳንድ አካባቢዎች በአንድ ቀን ተራዘመ


ፎቶ ሮይተርስ (ነሐሴ 23፣ 2023)
ፎቶ ሮይተርስ (ነሐሴ 23፣ 2023)

በዙምባብዌ ትናንት በተደረገው ምርጫ፣ በድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት እና በመዘግየት ምክንያት በአንዳንድ የምርጫ ክልሎች ድምጽ መስጠቱ በአንድ ቀን መራዘሙ ታውቋል።

የድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረቱ የተፈጠረው በገጠመው የሕግ ችግር ምክንያት መሆኑን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።

በአንድ የምርጫ ጣቢያ፣ ድምጽ አሰጣጡ መጠናቀቅ ከነበረበት አንድ ሰዓት በኋላም፣ ድምጽ መስጠት ያልተጀመረ እንደነበር የቪኦኤ ዘጋቢ ኮለምበስ ማቩንጋ መታዘብ ችሏል። መራጮች ከ12 ሰዓታት በላይ ድምጽ መስጫ ወረቀት ሲጠብቁ ቆይተዋል። ሁኔታው የታጠቁ አድማ በታኝ ፖሊሶች እንዲጠሩ አስገድዷል ተብሏል። የድምጽ መስጫ ሰዓቱ ካለፈ እና ሰዎች ወደየቤታቸው ከተበተኑ በኋላ ድምጽ አሰጣጡ እንደተጀመረ መራጮች ለቪኦኤ ተናግረዋል።

መዘግየቱ የተፈጠረው በገጠመው ከበድ ያለ የፍርድ ቤት ሙግት ምክንያት መሆኑን፣ የዚምባቡዌ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።

የወቅቱ ፕሬዝደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እና ዋና ተቀናቃኛቸው ኔልሰን ቻሚሳ በመዲናዋ ሃራሬ ድምጽ ሰጥተዋል።

የፕሬዝደንታዊ ምርጫ ውጤቱ ሰኞ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የፓርላማ መቀመጫ ውጤቶች ደግሞ፣ ድምጽ አሰጣጡ ባልዘገየባቸው ቦታዎች ከሐሙስ ጀምሮ እንደሚታወቁ ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG