በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሪጎዥን በአውሮፕላን አደጋ መሞታቸውን ሩሲያ አረጋገጠች


ዪቭጌኒ ፕሪጎዥን በዚህ በእ.አ.አ ነሐሴ 21፣ 2023 ከተለቀቀ ቪዲዮ ላይ በተቀነጨበ ፎቶ፣ በውል ባልታወቀ ስፍራ ለካሜሪ ሲናገሩ ያሳያል (ፎቶ AP ነሐሴ 21፣ 2023)
ዪቭጌኒ ፕሪጎዥን በዚህ በእ.አ.አ ነሐሴ 21፣ 2023 ከተለቀቀ ቪዲዮ ላይ በተቀነጨበ ፎቶ፣ በውል ባልታወቀ ስፍራ ለካሜሪ ሲናገሩ ያሳያል (ፎቶ AP ነሐሴ 21፣ 2023)

የቫግነር የግል ወታደራዊ ቡድን መሪ የሆኑት ዪቭጌኒ ፕሪጎዥን፣ ትናንት በተከሰከሰው አውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው እንዳለፈ የሩሲያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አረጋግጧል።

ፕሪጎዥን 10 ከሚሆኑትና ሕይወታቸው ካለፈው የአውሮፕላኑ ተጓዦች ውስጥ አንዱ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

በሩሲያ ወታደራዊ አዛዦች ላይ አመጽ ባስነሱ በሁለተኛው ወር ትናንት ሕይወታቸው ያለፈው ፕሪጎዥን፣ ከሞስኮ ወደ ሴንት ፒተርስበርግ በመብረር ላይ ሳሉ ነበር የግል አውሮፕላናቸው የተከሰከሰው።

አመጹ፣ አንዳንኔም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደርጎ የሚገለጸው ክስተት፣ ፕሪጎዥን ወደ ቤላሩስ እንደሚሄዱ ከተስማሙ በኋላ ተገቷል። ከዛ በኋላ ፕሪጎዥን ወደ ሩሲያ በተደጋጋሚ ይመላለሱ እንደነበር ታውቋል።

የቫግነር ወታደሮች፣ ባክሙትን ለመያዝ የተደርገውን ውጊያ ጨምሮ፣ በዩክሬን በነበሩ ከባድ ውጊያዎች ውስጥ ተሳትፈዋል።

ዛሬ ማለዳ፣ ሴንት ፒተርስበርግ በሚገኘው የቫግነር ቢሮ አቅራቢያ አበባ እና ሻማ ተቀምጦ ታይቷል።

በክሬምሊንም ሆነ በመከላከያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እስከአሁን በፕሪጎዥን አሟሟት ላይ የተሰጠ አስተያየት የለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG