በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገሮች ብሪክስን ተቀላቀሉ


የብሪክስ ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ (ፎቶ AP ነሐሴ 23፣ 2023)
የብሪክስ ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ (ፎቶ AP ነሐሴ 23፣ 2023)

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ አርጄንቲና፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ ኢራን እና ሳዑዲ ዓረቢያ ከመጪው የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት ጀምሮ ብሪክስ ተብሎ የሚጠራውን የበለጸጉ ሀገራት የኢኮኖሚ ስብስብን እንደሚቀላቀሉ ታውቋል።

ጆሃንስበርግ፣ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በተካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ላይ፣ የወቅቱ የስብስቡ ሊቀመንበር የሆነችው የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ ሀገራቱ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ መጋበዛቸውን አብስረዋል።

ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ በእ.አ.አ 2009 የመሠረቱትና፣ የሀገራቱን የመጀመሪያ ሆሄያት ይዞ የተሰየመው ብሪክስ፣ የዓለምን 40 በመቶ ሕዝብ እና አንድ አራተኛውን አጠቃላይ ምርት የያዘ ነው። በዓለም ከፍተኛ የነዳጅ አምራች የሆኑት ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ እና ኢራን አዲስ ከሚቀላቀሉት ሀገራት ውስጥ መሆናቸው የስብስቡን የኢኮኖሚ አቅም እና ድርሻ እንደሚጨምር ይጠበቃል።

በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ፍጥጫው ባየለበት ሁኔታ እና፣ በዩክሬን ላይ በምታካሂደው ጦርነት ምክያት ሩሲያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ቅራኔ መግባቷን በመመልከት፣ ብሪክስ በቻይና እና ሩሲያ ተጽእኖ ጸረ-ምዕራብ አቋም ይዟል የሚል ጥያቄ ይነሳበታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG