በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮጵያን ገበያ ሊቀላቀል ነው


ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮጵያን ገበያ ሊቀላቀል ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:30 0:00

በቅርቡ ለባለሀብቶች ክፍት የተደረገውን፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ የሚቀላቀል ሁለተኛ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ለመምረጥ፣ ዓለም አቀፍ ጨረታ እንዳወጣ፣ የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ። የቴሌኮም ኩባንያዎቹን ለመቆጣጠር፣ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ፣ የቁጥጥር ማኅቀፍ እና የአገልግሎት ጥራት ደረጃ መመሪያ እያዘጋጀ እንደሚገኝ፣ የመሥሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዲሬክተር አቶ ሚሊዮን ኀይለ ሚካኤል፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የአገልግሎት ጥራት መጓደል ሲያጋጥም፣ ደንበኞች ቅሬታቸውን ለባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የሚያቀርቡበት አሠራር እንደተዘረጋም አስታውቀዋል፡፡

የኩባንያዎቹ አገልግሎት፣ ትርፍ በሚያስገኙ አካባቢዎች ብቻ እንዳይታጠር የሚቆጣጠር፣ ጠንካራ ሥርዐት እንደተበጀም፣ ዋና ዲሬክተሩ ገልጸዋል።

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)

XS
SM
MD
LG