በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ከጦርነቱ ወዲህ 500 ሕፃናት በረኀብ እንደሞቱ ተነገረ


ሱዳን
ሱዳን

በሱዳን፣ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ሚያዝያ ወር ወዲህ፣ በዋና ከተማዪቱ ካርቱም፣ መንግሥት በሚያስተዳድረው የሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ የሞቱትን ከኻያ በላይ ሕፃናትን ጨምሮ፣ በመላ አገሪቱ፣ “ቁጥራቸው 500 የሚደርሱ ሕፃናት በረኀብ አልቀዋል፤” ሲል፣ አንድ ዓለም አቀፍ የረድኤት ቡድን ዛሬ አስታወቀ።

ዓለም አቀፉ የሕፃናት አድን ድርጅት (Save The Children) እንዳመለከተው፣ በሱዳን የነበሩትን 57 የመመገቢያ ማዕከላቱን ለመዝጋት ከተገደደበት ጊዜ አንሥቶ፣ “ከ31ሺሕ በላይ ሕፃናት፣ የምግብ እጥረት ለሚያስከትላቸውና ሌሎች ተዛማች በሽታዎች የሕክምና ርዳታን ይሻሉ፤” ብሏል።

በሱዳን የመንግሥት ኀይሎች እና በተቀናቃኙ ፈጥኖ ደራሽ ልዩ ኀይል ወታደሮች መሀከል የተቀሰቀሰው ውጊያ፣ ካርቱምንና ሌሎች ከተሞችን የጦር አውድማው ሲያደርግ፣ አብዛኛውን ነዋሪ፥ ለውኃ እና ለመብራት ዕጦት ዳርጓል፤ የጤና ጥበቃ ሥርዐቱም ሊፈርስ ከሚችልበት አፋፍ ማቃረቡ ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG