በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ሸዋ እና በደቡብ ወሎ ዞኖች በተደረጉ የተኩስ ልውውጦች ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ


በሰሜን ሸዋ እና በደቡብ ወሎ ዞኖች በተደረጉ የተኩስ ልውውጦች ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:03 0:00

በሰሜን ሸዋ እና በደቡብ ወሎ ዞኖች በተደረጉ የተኩስ ልውውጦች ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ

በዐማራ ክልል በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተስፋፋው ግጭት፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ በማጀቴ ከተማ እና በዙሪያው፣ እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ወግዲ ከተማ እና አካባቢው ጉድት መድረሱን ነዋሪዎች ገለፁ።

በግጭቱ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን፣ ለአካል ጉዳት ስለ መዳረጋቸው ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። በመሠረተ ልማቶች እና በግለሰቦች ንብረት ላይም ቁሳዊ ጥፋቶች ስለ መድረሳቸው፣ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡ ግለሰቦች ተናግረዋል፡፡

በማጀቴ ከተማ እና አካባቢው ያለው የግጭት ሁኔታ በውጊያው የቆሰሉትን ወደ ሕክምና ተቋማት ማድረስን አዳጋች እንዳደረገውና ወደ ግለሰቦች ቤቶች በማግለል ጭምር ለመስጠት እየተሞከረ እንደኾነ፣ የመረጃ ምንጮቹ ጠቅሰዋል፡፡

ከ15 ቀናት በፊት፣ በወግዲ ከተማ አካባቢ በነበረ ውጊያ፣ የደረሱበት የማይታወቅ ሰዎች ስለ መኖራቸውና ነዋሪው በጸጥታ ስጋት፣ በመንግሥታዊ አገልግሎት ዕጦት እና በኑሮ ውድነት እንደተቸገረም፣ አስተያየት ሰጭዎቹ አመልክተዋል፡፡ የወረዳው መንግሥታዊ መዋቅር ለጊዜው አገልግሎት እየሰጠ ባለመኾኑ፣ ደረሰ ስለተባለው ጉዳት፣ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አልተቻለም፡፡ ከዐማራ ክልል እና ፌደራል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ሓላፊዎች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG