ዋሽንግተን ዲሲ —
በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች፣ በሳዑዲ አረቢያ ድንበር ላይ ተገድለዋል፤ መባሉን፣ በጋራ እንደምትመረምር ኢትዮጵያ አስታወቀች።
የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች፣ ሕፃናትንና ሴቶችን ጨምሮ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን እንደገደሉ፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ ትላንት ባወጣው ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ድርጊቱን ከሳዑዲ መንግሥት ጋራ በመኾን፣ በአስቸኳይ እንደሚመረምር አስታውቋል።
አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ተመድ፣ “ክሡ አሳሳቢ ነው፤” ሲሉ፣ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በበኩሉ፣ “ክሡ መሠረት የሌለው ነው፤” ብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም