በቡዳፔስቱ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮንሺፕ ኢትዮጵያ በሴቶች 10ሺ ሜትር ውድድር ሁሉንም ሜዳሊያዎችን ጠራርጋ ወሰዳለች። ከፍተኛ ፉክክር የተያበትን ወድድር ጉዳፍ ጸጋዬ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ፣ የሀገሯ ልጆች ለተሰንበት ግደይ እና እጅጋሁ ታዬ ተከታትለው በመግባት "አረንጓዴው ጎርፍ" በሚል የመጠሪያ የሚታወቀውን የኢትዮጵያኑን የተነባበረ የስፖርት ዓለም ድል ታሪክ አስታውሰዋል።
በርካታ ኢትዮጵያዊያን የስፖርት አፍቃሪዎች ያስፈነደቀውን ድል አስመልክቶ ቡዳፔስት የሚገኘው ዘጋቢያችን ኤቢሳ ነገሰ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል፡፡