በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥረቶች ካልተሳኩ በኒጀር ወታደሮችን ለማዝመት መዘጋጀቱን ኢኮዋስ አስታወቀ።


ጥረቶች ካልተሳኩ በኒጀር ወታደሮችን ለማዝመት መዘጋጀቱን ኢኮዋስ አስታወቀ።
ጥረቶች ካልተሳኩ በኒጀር ወታደሮችን ለማዝመት መዘጋጀቱን ኢኮዋስ አስታወቀ።

የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) የዲፕሎማሲ ጥረቶች ካለተሳኩ በኒጀር ወታደራዊ አስተዳደር ላይ ጦር ለማዝመት መዘጋጀቱን የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች እና የደህንነት ኮሚሽነር አስታወቁ።

አብደል ፈታ ሙሳህ "ትዕዛዙ በሚሰጥበት በማንኛውም ጊዜ ለመሰማራት ዝግጁ ነን" ብለዋል በትናትናው ዕለት ። ለጊዜው ግልጽ የማይደረግ የዘመቻ ቀን እንደተቆረጠም ይፋ አድርገዋል ።

ይሁንና የኤኮዋስ መሪዎች ከጦርነት ድምጽ ይልቅ የዲፕሎማሲ ቋንቋን እንደሚመርጡ ጠቁመው ጉዳዩን ከወታደራዊው አመራር ጋር በዕርቅ ለመፍታት እና በህገ መንግስቱ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ባዞምን ወደ ኃላፊነታቸው ለመመለስ ወደ ኒያሚ በዛሬው ዕለት ዲፕሎማሲያዊ ልዑክ ሊላክ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ከኒጀር ወታደራዊ አስተዳደር እስካሁን ምላሽ አልተሰጠም ።

ባዙም ከስልጣን የተወገዱት በአውሮጳዊያኑ በሀምሌ 26 ሲሆን ፣ እስካሁን ድረስ ወታደራዊው አመራር ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን፣ የኢኮዋስን እና ሌሎችም አካላት ፕሬዚደንቱ ወደ ኃላፈነታቸው እንዲመለሱ ያቀረቡትን ጥሪ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱን ተከትሎ የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ተጠባባቂ ወታደራዊ ኃይል በኒጀር እንዲሰማራ ለማዘዝ ምክንያት ሆኖታል ።

15 አባላት ሀገራት ካሉት ማህበረሰብ አብዛኞቹ ወደ ኒጀር ለሚዘምተው ጦር አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ ናቸው። ይሄንን እርምጃ የሚቃወሙት በወታደራዊ አገዛዝ ስር ያሉት ሶስት አገሮች ማሊ ፣ ቡርኪናፋሶ እና ጊኒ እንዲሁም እራሷ ኒጀር ብቻ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG