በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአካል ጉዳት ያልበገራት አነቃቂዋ ጋዜጠኛ ፍሬ ሕይወት ታምሩ


የአካል ጉዳት ያልበገራት አነቃቂዋ ጋዜጠኛ ፍሬ ሕይወት ታምሩ 
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:24 0:00

የአካል ጉዳት ያልበገራት አነቃቂዋ ጋዜጠኛ ፍሬ ሕይወት ታምሩ 

በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በመርሐ ግብር አስተዋዋቂነት እና በጋዜጠኝነት ያገለገለችው ፍሬ ሕይወት ታምሩ፣ በአሁን ሰዓት ደግሞ፣ ሚሊ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን የተሰኘ ተቋም በመመሥረት፣ የተለያዩ ሥራዎችን ለሕዝብ እያደረሰች ትገኛለች።

ፍሬ ሕይወት፣ ከ10 ዓመት በፊት በደረሰባት የመኪና አደጋ የተነሣ፣ የቀኝ እግሯን አጥታለች፡፡ ከጊዜ በኋላ ባገኘችው ሰው ሠራሽ እግር፣ የዕለት ተዕለት ኑሮዋን የቀጠለችው ፍሬ ሕይወት፣ ጉዳቷ ሳይበግራት ለብዙዎች መነቃቃትን ለመፍጠር እየታተረች ትገኛለች።

በቅርቡም፣ በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማኅበር አማካይነት፣ “ፍሬ-ሕይወት” በሚል ስያሜ የተሠራውና በራሷ ታሪኳ ላይ የሚያጠነጥነው አጭር ፊልሟ፣ በአውስትሬሊያ በሚገኘው ዓለም አቀፉ “ፎከስ ኦን ኤቢሊቲ” የአጭር ፊልሞች ፌስቲቫል ላይ ለውድድር ቀርቧል።

ከአካል ጉዳቷ ይልቅ በአነቃቂ ክህሎቷ ላይ ያተኮረችው ፍሬ ሕይወት ታምሩ፣ በሥራዋ ላይ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርጋለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG