በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭት የሰነበቱት የዐማራ ክልል ከተሞች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሱ ናቸው


በግጭት የሰነበቱት የዐማራ ክልል ከተሞች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሱ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:24 0:00

ሰሞኑን፣ በመከላከያ ሠራዊቱ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል፣ በትጥቅ የተደገፈ ግጭት ተካሒዶባቸው የነበሩ የዐማራ ክልል ከተሞች፣ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሱ እንደኾኑ፣ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የክልሉን ዋና መዲና ባሕር ዳርን ጨምሮ፣ በጎንደር፣ በፍኖተ ሰላም፣ በሸዋሮቢት እና በሌሎችም ከግጭቱ የወጡ ከተሞች፣ ዛሬ ረቡዕ፥ የንግድ ተቋማት እንደከተፈቱ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተጀመረና በጥቅሉ ሰላማዊ ድባብ እንደሰፈነ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የከተሞቹ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ፣ የክልሉ ዋና ዋና ከተሞች፣ ከቀናት ተኩስ እና ግጭት በኋላ ወደ መረጋጋት እንደተመለሱ ገልጿል፡፡ የመንግሥት መግለጫዎችንም ጠቅሶ፣ እስከ ስድስት ወራት ሊዘልቅ የሚችለው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ የተፈጻሚነቱ ቦታ ውስንና ወቅቱም የአጠረ እንዲኾን መጠየቁ አይዘነጋም።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG