በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በክልላዊ ግጭቶች ከስጋትያልወጣው የኢትዮጵያ ቱሪዝም የግብር እፎይታንና መንግሥታዊ ማበረታቻዎችን እንደሚሻ ተገለጸ


የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ጫና ተቋቁሞ በማገገም ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ፣ መነሻውን በትግራይ ክልል አድርጎ ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና በየአካባቢው በሚፈጠሩ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች፣ ይብሱን እየቀጨጨ እንዳለ፣ የመስኩ ባለሞያዎች ይናገራሉ።

በጥቅምት ወር መጨረሻ፣ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ላይ የተደረሰው በዘላቂነት ተኩስ የማቆም የሰላም ስምምነት፣ መጠነኛ ተስፋ እና መነቃቃት ሲፈጥር፣ የክልል ልዩ ኀይሎችን ዳግም አደረጃጀት መንሥኤ ካደረገው ተቃውሞ ጋራ ተያይዞ፣ ሰሞኑን በዐማራ ክልል የተስፋፋው ግጭት በአንጻሩ፣ የዘርፉን ተዋንያን ዳግም ከስጋት ላይ ጥሏል።

ግጭቶቹ ያስከተሏቸው የመሠረተ ልማት ውድመቶች፣ የሰዎች መፈናቀል፣ እንዲሁም የማኅበረ ፖለቲካ አለመረጋጋት ባደቀቀው የቱሪዝሙ ዘርፍ፣ ከኮቪድ-19 የዝግ ወቅት አንሥቶ፣ አንዳችም ማበረታቻም ኾነ የግብር እፎይታ እንዳላገኙ አስጎብኚ ድርጅቶቹ ይናገራሉ፡፡

የዘርፉ ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ ብዙ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጭዎች፣ ድርጅቶቻቸውን እየዘጉ ባሉበት በዚኽ የቀቢጸ ተስፋ ኹኔታ፣ መንግሥት፣ ይበልጥል ሊጎዳ የሚችል የግብር መመሪያ እና ሕጎችን ከማውጣት መታቀብ እንደሚገባው ይናገራሉ፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG