በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት በታንዛንያ የታሰሩ አምስት ሺሕ ኢትዮጵያን ፍልሰተኞችን እንደሚያስመልስ ገለጸ


መንግሥት በታንዛንያ የታሰሩ አምስት ሺሕ ኢትዮጵያን ፍልሰተኞችን እንደሚያስመልስ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:31 0:00

በታንዛንያ የታሰሩ አምስት ሺሕ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ እንደተዘጋጀ፣ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ጥግይበሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ በታንዛኒያ እስር ቤቶች የሚገኙትን አምስት ሺሕ ዜጎችን አስመልክቶ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውይይት ሲካሔድ ቆይቶ እንደተጠናቀቀና እስረኞቹን ወደ ሀገራቸው ለማጓጓዝም ዝግጅት እየተደረገ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

በየዓመቱ እስከ 200ሺሕ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን፣ ወደተለያዩ ሀገራት በሕገ ወጥ መንገድ እንደሚሰደዱ ሐላፊው አውስተው፣ በጉዟቸውም፣ እስር እና የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው አመልክተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG