በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሚዋቀረው “የማዕከላዊ ኢትዮጵያ” ክልል የቢሮዎች ድልድልን የሚቃወም ከቤት ያለመውጣት አድማ ተደረገ


በሚዋቀረው “የማዕከላዊ ኢትዮጵያ” ክልል የቢሮዎች ድልድልን የሚቃወም ከቤት ያለመውጣት አድማ ተደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00

እየተዋቀረ በሚገኘው “የማዕከላዊ ኢትዮጵያ” ክልል፣ የሥራ አስፈጻሚ ቢሮዎችን ድልድል የሚቃወም ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ፣ በከምባታ ጠምባሮ ዞን የዱራሜ፣ የአንጋጫ እና የዳንቦያ ከተማ ነዋሪዎች ተደረገ፡፡

የከተሞቹ ነዋሪዎች፣ ትላንት እና ዛሬ ያደረጉት ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ መነሻ፣ እንደ ዐዲስ በሚዋቀረው “የማዕከላዊ ኢትዮጵያ” ክልል ፣ ሰሞኑን እንደተካሔደ የተሰማው፣ የሥራ አስፈጻሚ ቢሮዎች ድልድል፣ “ኢ-ፍትሐዊ በመኾኑ ነው፤” ሲሉ ተናግረዋል።

የዞኑ ምክር ቤትም፣ ከትላንት በስቲያ ባካሔደው አስቸኳይ ጉባኤ፣ ተደረገ የተባለውን ድልድል የተቃወመ ሲኾን፣ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ በመስማማት፣ ውሳኔውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደላከ፣ የምክር ቤቱ አባላት ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ገልጸዋል።

የደቡብ ክልል መንግሥት፣ የዞኑን ምክር ቤት ውሳኔም ኾነ የነዋሪዎችን ተቃውሞ አስመልክቶ፣ ያለው ነገር የለም፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG