በዳርፉር በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የተሰነዘረ ጥቃትን ተከትሎ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ዋና ከተማዋን ንያላ ለቀው መውጣታቸውን ነዋሪዎች ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል። የተተኮሱ ሮኬቶች መኖሪያ ቤቶች ላይ አርፈዋል ሲሉ ነዋሪዎቹ ጭምረው ገልጸዋል።
ዳርፉር እና የሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በሀገሪቱ ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የሱዳን ሁለተኛ ከተማ እና የምዕራብ ዳርፉር ዋና ከተማ ከሆነችው ንያላ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ለቀው በመውጣት ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በሱዳን ግጭቱ ሚያዚያ 7 ከጀመረ ወዲህ፣ 3ሺሕ 900 ሰዎች እንደሞቱ ‘የትጥቅ ግጭት አካባቢዎች ዳታ ፕሮጀክት’ የሰኘው ተቋም አስታውቋል።
ተመድ በበኩሉ ከ4ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል።
ዳርፉር በታሪኳ ከፍተኛ ደም መፋሰስን አይታለች። ከሃያ ዓመታት በፊት የቀድሞው ፕሬዝደንት ኦማር አል በሽር፣ አረብ ያልሆኑትን ሱዳናውያን ለማጥፋት በሚል የአረብ ጎሳ ሚሊሺያዎችን እንዲዘምቱ አድርገው ክፍተኛ እልቂት ተፈጽሟል።
አሁንም በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እና በአረብ ሚሊሺያዎች እልቂት በመፈጸም ላይ ነው ሲሉ የተለያዩ ወገኖች ክስ ያሰማሉ።
መድረክ / ፎረም