በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእንግሊዝ የባህር ወሽመጥ በደረሰ የጀልባ አደጋ ፍልሰተኞች ሞቱ


ከአደጋው ከተረፉት ፍልሰተኞች በከፊል (ፎቶ ሮይተርስ ነሐሴ 12, 2023)
ከአደጋው ከተረፉት ፍልሰተኞች በከፊል (ፎቶ ሮይተርስ ነሐሴ 12, 2023)

አንድ ሕጻንን ጨምሮ ቢያንስ ሁለት ቱኒዚያን በሀገሪቱ ባህር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ የባህር ድንበር ጠባቂ ኃይሉ አስታውቋል።

ጀልባዋ 20 የሚሆኑ የቱኒዚያ ፍልሰተኞችን ይዛ ወደ አውሮፓ ለማቅናት ሙከራ ላይ ነበረች። ከመነሳቷ ጥቂት እንደቆየች መገልበጧን የባህር ድንበር ጠባቂ ኃይሉ ገልጿል።

የአንድ የ20 ዓመት ጎልማሳ እና የአንድ ጨቅላ ሕጻን አስከሬን ማግኘቱን ኃይሉ አስታውቋል።

13 ፍልሰተኞች ሲገኙ፣ አምስት የሚሆኑትን ለማግኘት ፍለጋው ቀጥሏል።

በዚህ ዓመት ብቻ በሜዲትሬንያን ባህር ላይ ወደ አውሮፓ ለምሻገር የሞከሩ 1ሺሕ 800 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን እንዳጡ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM አስታውቋል።

በተያያዥ ዜና፣ 65 ፍልሰተኞችን ይዞ በእንግሊዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ትናንት ተገልብጦ ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ሁለት ፍልሰተኞች የደረሱበት አልታወቅም ተብሏል።

አልፎ ሂያጅ መርከብ አደጋው መድረሱን ማስታወቁን ተከትሎ፣ የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ አደጋ ሰራተኞች በስፍራው ደርሰዋል።

ስድስቱ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡት የአፍጋኒስታን ዜጎች እንደሆኑ የቢቢሲ ዘገባ አምልክቷል።

ከፈረንሳይ በመነሳት የእንግሊዝ የባሕር ወሽመጥን አቋርጠው ወደዛች ሀገር ለመግባት ፍልሰተኞች አደገኛውን ጉዞ ያደርጋሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG