በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊላንድ ግጭት 9 የፖሊስ ዓባላት ተገደሉ


በራስ ገዟ ሶማሊላንድ ከተቃዋሚው ሚሊሺያ ጋር በተደረገ ውጊያ ዘጠኝ የፖሊስ ዓባላት መገደላቸው ታውቋል።

ከመዲናዋ ሃርጌሳ 95 ኪሜ ርቀት ላይ በተደረገው ውጊያ፣ 30 የሚሆኑ የፖሊስ ዓባላትን በደፈጣ ካጠቁ በኋላ፣ ዘጠኙን ገድለዋል ተብሏል።

‘ዋዳኒ’ በመባል የሚጠራው ዋናው የተቃዋሚ ፓርቲ ለጥቃቱ ተጠያቂ እንደሆነ የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሞሃመድ አህመድ ተናግረዋል። የፓርቲው መሪ አብድራህማን ኢሮ ሚሊሺያዎቹን አስጠግተዋል ሲሉ ከሰዋል። ኢሮ ክሱን አስተባብለው፣ ሁሉም ኃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ ጥሪ አድርገዋል።

ቀድሞ በእንግሊዝ ጥበቃ ሥር ትደዳደር የነበረችው የሶማሊላንድ ግዛት ከእ.አ.አ 1992 ጀምሮ ከሶማሊያ ነጻነቷን ብታውጅም፣ ዓለም እውቅና አልሰጣትም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG