በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሐዋይ ደሴት የእሳት አደጋ ሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው


በሐዋይ እሳት ያደርሰው አደጋ በከፊል (ፎቶ ኤኤፍፒ ነሐሴ 11,2023)
በሐዋይ እሳት ያደርሰው አደጋ በከፊል (ፎቶ ኤኤፍፒ ነሐሴ 11,2023)

በአሜሪካ፤ በማዊ-ሐዋይ ደሴት በዚህ ሳምንት በተነሳው የእሳት አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እስከ ትናንት ምሽት 93 መድረሱ ታውቋል። ባለሥልጣናት ለዜና ሰዎች እንደተናገሩት ከሆነ፣ የሟቾች ቁጥር ከተጠቀስውም ሊጨምር ይችላል።

በደሴቲቱ ሐዋይ የተነሣው የእሳት ቃጠሎ በፍጥነት በመዛመቱ፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው ሸሽተዋል።

የደሴቲቱ ፖሊስ አዛዥ እንደተናገሩት፣ በውሻ እየተረዱ ያደረጉት አሰሳ እስከ አሁን የሸፈነው 3 በመቶ የሚሆነውን አካባቢ ብቻ ነው። በመሆኑም የሟቾች ቁጥር መጨመሩ የማይቀር መሆኑን ተናግረዋል።

እሳቱ፣ ጥንታዊ የሆነችውንና የቱሪስት መዳረሻ የኾነችው ላሃይና ከተማ፣ ሙሉ በሙሉ አውድሟል።

የከተማዋ ነዋሪዎች፣ እሳቱ በፍጥነት በሚዛመትበት ወቅት በአደጋ ማስጠንቀቂያው እንዲያውቁ እንዳልተደረገ በመናገር ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG