በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢኳዶሩ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ግድያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ


በኢኳዶሩ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ግድያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:50 0:00

ኢኳዶር ባለፈው ረቡዕ ከተገደሉት ፕሬዝዳንታዊ እጩ ፈርናንዶ ቪያቪሴንሲዮ ግድያ ጋር በተያያዘ ስድስት የኮሎምቢያ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አዋለች።

ተጠርጣሪዎቹ ከፖሊስ ጋር የተኩስ ልውውጥ ባደረጉበት ወቅት የቆሰለ አንድ ሌላ ተጠርጣሪ ኮሎምቢያዊም ህይወቱ ማለፉ ታውቋል።

የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎችን በመቃወም የሚታወቁት ቪያቪሴንሲዮ የግድያ ዛቻ ይደርሳቸው እንደነበር ተዘግቧል።

የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሁዋን ዛፓታ ሲናገሩት “የብሔራዊ ፖሊሶች የዚህ አስጸያፊ ድርጊት አውጠንጣኝ የሆኑ ግለሰቦች የመጀመሪያ እስር ፈጽመዋል። የዚህን ወንጀል መንስኤ እና ድርጊቱን በማውጠንጠኑ ሥራ የተሳተፉትን በሙሉ ለመቆጣጠር ሙሉ የተግባር እና የምርመራ አቅማቸውን ይጠቀማሉ” ብለዋል ።

የኢኳዶሩ ፕሬዝዳንት ጊለርሞ ላሶ በበኩላቸው ‘ግድያው ኢኳዶር ከዘጠኝ ቀናት በኋላ የምታካሂደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከማከናወን አያግዳትም’ ብለዋል።

ላስሶ በቪያቪሴንሲዮ ግድያ ምርመራ እንዲያግዛቸው የዩናይትድ ስቴትሱን ብሔራዊ የወንጀል ምርመራ ቢሮ FBI’ን እርዳታ ጠይቀዋል። የኤፍቢአይ መርማሪ ቡድንም በቅርቡ ኢኳዶር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG