በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዊ-ሐዋይ ደሴት የእሳት አደጋ ቢያንስ 36 ሰዎች ሞቱ


እሳቱ፣ ጥንታዊ ሕንፃዎች በሚገኙባትና የቱሪስት መዳረሻ በኾነችው ላሃይና ከተማ፣ መኪኖችንና ሌሎች ንብረቶችን አጋይቷል
እሳቱ፣ ጥንታዊ ሕንፃዎች በሚገኙባትና የቱሪስት መዳረሻ በኾነችው ላሃይና ከተማ፣ መኪኖችንና ሌሎች ንብረቶችን አጋይቷል

በደሴቲቱ ሐዋይ፣ የተነሣ የእሳት ቃጠሎ በፍጥነት በመዛመቱ፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው እየሸሹ ናቸው።

እሳቱ፣ ጥንታዊ ሕንፃዎች በሚገኙባትና የቱሪስት መዳረሻ በኾነችው ላሃይና ከተማ፣ መኪኖችንና ሌሎች ንብረቶችን ሲያጋይ፣ የእሳት አደጋ ሠራተኞች ደግሞ ቃጠሎውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በመረባረብ ላይ ናቸው።
11 ሺሕ የሚደርሱ አገር ጎብኚዎች፣ ትላንት ረቡዕ፣ ደሴቲቱን ለቀው እንደወጡ ሲታወቅ፣ ተጨማሪ 1 ሺሕ 500 የሚኾኑቱም፣ ዛሬ እንደሚወጡ ይጠበቃል።
እሳቱ በፍጥነት እየተግለበለበ በመዛመት ላይ በመኾኑ፣ ሕይወታቸውን ሊያጡ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል፣ ባለሥልጣናት እየተናገሩ ናቸው፤ ሲል የአሶሺዬትድ ፕረስ ሪፖርት አመልክቷል።

የቃጠሎው መንሥኤ በትክክል ባይታወቅም፣ በአካባቢው ያለው ከፍተኛ ነፋስ እና ዝቅተኛ ርጥበት፣ እሳት ሊፈጥር እንደሚችል፣ የአየር ትንበያ ባለሞያዎች ሲያስጠነቅቁ እንደነበር ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG