በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኢትዮጵያ እየተበላሸ የመጣው የጸጥታ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለፀ


ፎቶ ፋይል: የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ
ፎቶ ፋይል: የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፣ “በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በተለይም በዐማራ ክልል እየተበላሸ የመጣው የጸጥታ ሁኔታ አሳስቦኛል” ሲል ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

የባለሞያዎቹ ቡድን በተጨማሪም፣ “ሐምሌ 28 ቀን 2015 በሚኒስትሮች ም/ቤት የወጣው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በሕገ መንግስቱ መሠረት በተወካዮች ም/ቤት መጽደቅ እንደነበረበት ተገንዝቧል” ብሏል።

“ከዚህ በፊት ይወጡ የነበሩ የአስቸኳይ ግዜ ዐዋጆች፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን ያሰከተሉ ነበሩ” ያለው ኮሚሽኑ፣ መንግሥት ግዴታው በሆነው የዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች አንቀጽ 4 ድንጋጌዎች መሠረት ‘አስፈላጊ፣ የተመጣጠነ፣ እና ያላደላ’ የሚሉትን መርሆች እንዲከተል ጠይቋል።

ኮሚሽኑ በተጨማሪም፣ ሁሉም ወገኖች የስብዓዊ መብቶችን እንዲያከብሩ፣ ሁኔታዎችን ለማርገብ ጥረት እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም ለሰላማዊ መፍትሄ ቅድሚያ እንዲሰጡ ጠይቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG