በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በቻይና የአሜሪካንን የቴክኖሎጂ ሙዓለ ነዋይ የሚገድብ መመሪያ ፈረሙ


ፋይል - ሁዋያን በተሰኘ የቻይና ከተማ የሚገኘው ጃንሱ አዠር ተቋም ውስጥ ሰራተኞች በከፊል አስተላላፊ የሆነ ቺፕ ምርት ላይ ሲሰሩ
ፋይል - ሁዋያን በተሰኘ የቻይና ከተማ የሚገኘው ጃንሱ አዠር ተቋም ውስጥ ሰራተኞች በከፊል አስተላላፊ የሆነ ቺፕ ምርት ላይ ሲሰሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የኮምፒዩተር ቺፕ እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን አስመልክቶ፣ የአገራቸው ሙዓለ ነዋይ በቻይና ፈሰስ እንዳይደረግ የሚገድብ መመሪያ፣ ትላንት ፈርመዋል። ይህም፣ በሁለቱ ታላላቅ ኢኮኖሚዎች መሀከል ውጥረቱን እንደሚያባብስ ተነግሯል።

እገዳው፥ ሰሚኮንዳክተሮችን፣ ኳንተም ቴክኖሎጂንና ሰው ሠራሽ አእምሮን የሚያካትት ነው፡፡ በእነዚኽ ቴክኖሎጂዎች መስክ፥ አሜሪካ፣ ጃፓንና ኔዘርላንድ፣ በፊተኛው መሥመር ሲገኙ፣ ቻይና በበኩሏ፣ አገራዊ አማራጭ በማበልጸግ ላይ እንደኾነች የሮይተርስ ሪፖርት ጠቁሟል።

ባይደን የፈረሙት ትዕዛዝ፣ በቴክኖሎጂው ዘርፍ፣ ከአሜሪካ ወደ ቻይና የሚፈሰውንና አገሪቱ ጦሯን ለማዘመን ልትጠቀምበት የምትችለውን ሙዓለ ነዋይ ለማስቆም ያለመ ነው፤ ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ፣ ውሳኔው ላይ ከመድረሳቸው አስቀድሞ፣ ከአጋር ሀገራት ጋራ መምከራቸውንና የቡድን ሰባት አባሎችንም ሐሳብ እንዳካተቱ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG