በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል ግጭት በዳባት ሽመላኮ መጠለያ የሚገኙ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ዳግም ተፈናቀሉ


በዐማራ ክልል ግጭት በዳባት ሽመላኮ መጠለያ የሚገኙ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ዳግም ተፈናቀሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:02 0:00

በዐማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ፣ “ሽመላኮ” በተሰኘው መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች፣ በመከላከያ ሠራዊቱ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ፣ ጣቢያው ላይ ጉዳት በመድረሱ ዳግም እንደተፈናቀሉ ገለጹ።

ቤተሰቦቻቸው የጠፉባቸው ተፈናቃዮች ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ከሁለት ቀናት በፊት በአካባቢው በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፣ ተተኳሽ በጣቢያው ውስጥ እንደወደቀና መጠለያውን ትተው ጫካ እንደገቡ ገልጸዋል፡፡

ከአካባቢው ባለሥልጣናት እና ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM) ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

XS
SM
MD
LG