በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ዲፕሎማት የኒዤር መፈንቅለ መንግሥት መሪዎችን አነጋገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ዲፕሎማት የኒዤር መፈንቅለ መንግሥት መሪዎችን አነጋገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:09 0:00

የኒዤር ወታደራዊ ሁንታ መሪዎች፣ ዐዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፕሬዚዳንታዊ ጥበቃ ዘብ አዛዥ እንደሾሙ፣ በዛሬው ዕለት ይፋ ሲያደርጉ፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ቪክቶሪያ ኑላንድ ደግሞ፣ ትላንት ሰኞ፣ ወደ ኒያሜ ተጉዘው፣ ዐዲሶቹን የኒዤር ወታደራዊ መሪዎች አነጋግረዋል።

የሁንታው መሪዎች ዐዲስ ባለሥልጣናትን የሾሙት፣ ፕሬዚዳንት መሐመድ ባዙምን ወደ ሥልጣን እንዲመልሱ የተያዘው ዓለም አቀፍ ግፊት በርትቶ በቀጠለበት በዚኽ ወቅት ነው።

ሁንታው፣ ሥልጣን ለፕሬዚዳንቱ እንዲያስረክብ፣ ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ማኅበረሰብ(ኤኮዋስ) የተሰጠውን፣ የእሑዱን የጊዜ ገደብ ሳያከብር መቅረቱንና ክፍለ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ማኅበረሰቡም፣ ያስጠነቀቀውን ያህል ወታደራዊ ርምጃ ሳይወስድ መቅረቱን ተከትሎ፣ የኒዤርን ኹኔታ በቅርበት እየተከታተለች ያለችው ዋሽንግተን፣ የምትሰጣትን ርዳታ በጊዜያዊነት እንዳቆመች አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG