በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጡ ቀጥሏል


በዐማራ ክልል በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጡ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:00 0:00

የክልሉን ዋና መዲና ባሕር ዳር ከተማን ጨምሮ፣ በዐማራ ክልል በርካታ ሥፍራዎች፣ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል፣ እየተደረገ ያለው የተኩስ ልውውጥ መቀጠሉን፣ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የተኩስ ልውውጡ፣ በሰላማዊ ሰዎችም ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ፣ አስተያየት ሰጪዎች ለአሜሪካ ድምፅ አብራርተዋል፡፡

በተያያዘ፣ በዐማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች፣ “አንዳንድ የዞንና የወረዳ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን” የገለጹት፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዲሬክተር ጀነራል እና የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ዕዙ፥ ክልሉን በአራት ኮማንድ ፖስቶች ከፍሎ ርምጃ እንደሚወስድ አብራርተዋል፡፡

ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በኋላ፣ በዐዲስ አበባ ከተማ፣ የተለያዩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ እንደኾነ፣ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የተለያዩ አካላት የሰላም ጥሪ በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡በክልሉ ያለው ግጭት እንዳሳሰባቸው የገለጹት፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዲሬክተር ዶር. ቴድሮስ አድኀኖም፣ መንገዶች መዘጋታቸው እና ኢንተርኔት መቋረጡ፣ የሰብአዊ ተደራሽነትን አስቸጋሪ እንዳደረገ በመጥቀስ፣ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG