በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስዊድን ዩናይትድ ስቴትስን በመለያ ምት አሸነፈች


በሜልበርን አውስትራሊያ የሴቶች የአለም ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታ የጥሎ ማለፍ ውድድር ዩናይትድ ስቴትስን በመለያ ምት ያሸነፉት የስዊድን ተጫዋቾች ደስታቸውን ሲገልጹ ፣ እኤአ ነሀሴ 6 2023
በሜልበርን አውስትራሊያ የሴቶች የአለም ዋንጫ የእግር ኳስ ጨዋታ የጥሎ ማለፍ ውድድር ዩናይትድ ስቴትስን በመለያ ምት ያሸነፉት የስዊድን ተጫዋቾች ደስታቸውን ሲገልጹ ፣ እኤአ ነሀሴ 6 2023

በዓለም የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ውድድር ዛሬ ስዊድን ዩናይትድ ስቴትስን 5 ለ4 በሆነ የመለያ ምት አሸነፈች፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በዛሬው እሁድ ጨዋታቸው በተጨማሪው ሰዐት ሳይቀር ዜሮ ለዜሮ ሆነው ባለመሸናነፋቸው የመለያ ምት ተሰጥቷል፡፡

የስዊድን ተጫዋችዋ ሊና ኸርቲግ የመታቻት አወዛጋቢ ኳስ በዩናይትድ ስቴትስ በረኛ ከመረቡ ሳትደርስ ተርፋለች፡፡ ይሁን እንጂ በረኛዋ ከአየር ደልቃ ወደ ውጭ የመለሰቻት ኳስ ከጎሉ መስመር ወደ ውስጥ ዘልቃ መግባቷ በድጋሚ ማጣራት ተረጋግጦ ስዊድን አሸናፊ ሆናለች፡፡

ዩናይትድ ስቴትሷ ሶፊያ ስሚዝ ለአራተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት የማድረግ እድል ብታገኝም ጎሉን በመሳት ኳሷን ከጎሉ አናት ወደ ውጭ ልካለች፡፡

የስዊድን በረኛ ዘኪራ ሙሶቪክ በዩናይትድ ስቴትስ የተሞከሩ 11 ያለቀላቸው ጎሎችን በማትረፏ ጀግና ተብላለች፡፡

በትናንቱ ጨዋታ ኔዘርላንድ ደቡብ አፍሪካን 2 ለ0 አሸንፋለች፡፡

እንግሊዝ እና ናይጄሪያ፣ ዴንማርክ ከአውስትራሊያ ዛሬ ሌሊቱን ይገጥማሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG