በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በዩጋንዳ የሰብዓዊ መብት ተልዕኮውን አቆመ


የዩጋንዳ መሪ ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ
የዩጋንዳ መሪ ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጽ/ቤት በዩጋንዳ የሚገኘውን ቢሮውን ለመዝጋት መገደዱን አርብ ዕለት ያስታወቀ ሲሆን ከዛሬ ቅዳሜ አንስቶ ያለውን ተልዕኮ ማቆሙን ጨምሮ ገልጿል።

የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ “በዩጋንዳ ያለውን ቢሯችንን ከ18 ዓመታት በኋላ ልንዘጋ መሆኑን ሳስታውቅ ሀዘን ይሰማኛል” ያሉ ሲሆን “በእነዚህ ዓመታት ከተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰቦች፣ በተለያዩ የህይወት ዘርፎች ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር በጋራ በመስራት እንዲሁም ከሀገሪቱ ብሔራዊ የዩጋንዳዊያን የሰብዓዊ መብት እና ደህነንት ቢሮ ጋር ስንሰራ ቆይተናል” ብለዋል።

የዋና ኮሚሽነሩ ቃል አቀባይ የሆኑት ራቪና ሻምዳሳኒ የዩጋንዳ መንግስት ለዋና ኮሚሽነሩ ባለፈው የካቲት ወር ላይ ከዚህ በኋላ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ቢሮ በሀገሪቱ እንዲሰራ የሚፈቅደውን ስምምነት አናድስም ሲሉ አስታውቀዋል በማለት ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG