በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምዕራብ አፍሪካ ወታደራዊ መሪዎች አዲሱን አካሄዳቸውን አስታወቁ


የኒጀር መፈንቅለ መንግስት 2015
የኒጀር መፈንቅለ መንግስት 2015

የኒጀር መፈንቅለ መንግስት መሪዎች የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ኤኮዋስን ዛቻ በኃይል አጸፋ እንደሚመልሱ አስጠነቀቁ። መሪዎቹ ምንም ዓይነት ወደኋላ የማለት ምልክት አላሳዩም። ማስጠንቀቂያው የመጣው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባቸውን ቡርኪናፋሶ እና ማሊን “ከታገዱ ወዳጅ ሀገሮች” በስተቀር በሚል በመለየት ነው።

ሐሙስ ዕለት ማምሻው ላይ የጁንታው ቃል አቀባይ አማዱ አብድራማኔ ከኒጀር የቀድሞ ቅኝ ገዥ፤ ፈረንሳይ ጋር የሁለትዮሽ ወታደራዊ ስምምነቶችን ማቆማቸውን በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በመቅረብ አንብበዋል። ፈረንሳይ በመላው ኒጀር 1,500 የሚደርሱ ሽብርን የሚዋጉ ወታደሮች አሏት።

አብድራማኔ በመግለጫው አያይዘውም በኒጀር ፕሬዘዳንት የተሰየሙ እና የኤኮዋስን የውይይት ጥረት እየመሩ ያሉ የፈረንሳይ፣ የዩናይትድ ስቴትስ፣ የቶጎ እና የጎረቤት ሀገር ናይጄሪያ መንግስታት አምባሳደሮች ውክልና መሻሩን አስታውቀዋል።

መፈንቅለ መንግስቱ በአፍሪካ ህብረት፣ በምዕራባውያን መንግስታት እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበታል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን የኒጀር ፕሬዘዳንት ባውዛም በአፋጣኝ እንዲለቀቁ የጠየቁ ሲሆን በኒጀር የተፈጠረው ሁኔታ “ዴሞክራሲ ላይ የተደቀነ ትልቅ ተግዳሮት” ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ አንዳንድ ረድኤት ድጋፎችን ለኒጀር መንግስት መስጠቷን አቋርጣለች ብለዋል።

በተያያዘ በመንግስታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ግሪንፊልድ “መፈንቅለ መንግስቱ ተቀባይነት የሌለው ነው” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “በቀጠናው ይሄን ነገር ለመከላከል እንሰራለን” ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።

አምባሳደሯ አክለውም ዩናይትድ ስቴትስ “አንዳንድ አሜሪካዊያን ዜጎን ለማስወጣት” በሂደት ላይ ትገኛለች ሲሉ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG